#AddisAbabaPoliceCommission

በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስና በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ቅንጅት በጥቁር ገበያ ሊሸጥ የነበረ ሽጉጥና የተለያዩ ጥይቶችን ከእነ ተጠርጣሪዎቹ እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡

ከእህል ጋር ተደባልቆ ወደ ክልል ሊጓጓዝ የነበረ ጥይትም በህብረተሰቡ ትብብር መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ሁለቱ አካላት ከህብረተሰቡ በደረሳቸው መረጃ መሰረት ባደረጉት ክትትል ሦስት ግለሰቦች በቢጫ ታክሲ፦
- 25 ቱርክ ሰራሽ ኢኮልፒ ሽጉጥ ፣
- 586 ፍሬ የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣
- 69 ፍሬ የብሬን ጥይት በጥቁር ገበያ በመገበያየት ላይ እንዳሉ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ዘነበወርቅ አካባቢ ሀምሌ 28 ቀን 2013 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ ሀምሌ 23 ቀን 2013 አንድ ግለሰብ 730 ፍሬ የክላሽን ኮቭ ጥይት ከገብስ ጋር በመቀላቀል ወደ ስልጤ ዞን ለማዘዋወር ሲሞክር በዘነበ ወርቅ መናኸሪያ ተይዟል፡፡

በጥቁር ገበያ የጦር መሳሪያ ሲገበያዩ የተገኙት ሦስት ተጠርጣሪዎችና የክላሽን ኮቭ ጥይት ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ ታስረው ጉዳያቸው እየተጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopia