#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። ሚኒስትሯ በዛሬ መግለጫቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተሰጠ ስላለው ስለኮቪድ-19 ክትባት መረጃ ሰጥተዋል።

ዶክተር ሊያ ታደሰ እስካሁን ከ2 ሚሊየን በላይ ዜጎች የመጀመሪያ ዙር ክትባት እንደወሰዱ ከ42 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ የሁለተኛው ዙር ክትባት እንደወሰዱ አሳውቀዋል።

ክትባቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በተከሰተ እጥረት መዘግየቱን ያነሱ ዲሆ በቅርቡ 400 ሺህ የሚጠጋ የአስትራዜኒካ ክትባት ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል ብለዋል።

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከአርብ ጀምሮ ደግሞ በክልሎች የመጀመሪያውን ክትባት ከወሰዱ 3 ወር የሞላቸው ዜጎች ክትባቱን መውሰድ ይችላሉ ሲሉ ገልፀዋን።

ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ክትባቶችን ለማግኘት የማፈላለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህኛው ዙር ክትባት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ዜጎች ዝርዝር ፦

• የትራንስፖርት ዘርፍ ሰራተኞች ( የአውቶብስ እና የሚኒባስ ሹፌሮች)፣
• የመንግስትና የግል ባንኮች ሰራተኞች፣
• የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ቢሮዎች ሰራተኞች፣
• የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የማረሚያ ቤቶችና የፍርድ ቤቶች ሰራተኞች
• የውልና ማስረጃ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች፣
• መምህራን የህጻናት ማቆያ የመደበኛና የኮሌጅ መምህራን፣
• የሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰራተኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ሰራተኞች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

NB : የመጀመሪያ ዙር ክትባት የሚወስዱ ዜጎች ሁለተኛው ዙር ክትባት ከ3 እስከ 4 ሳምንት ስለሚሰጥ ዜጎች ክትባቱን እንዲወስዱም ዶ/ር ሊያ ታደሰ መልዕክት አስተላልፈዋል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia