#HachaluHundessa

አዲሱ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ “ማል መሊሳ (Maal Mallisaa) የሙዚቃ አልበም በዓለም አቀፉ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በiTunes ወርልድ ቻርት ሽያጭ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አልበሙ እስከ ትናንት ባለ መረጃ በተለቀቀ በሁለት ቀናት ውስጥ ነው 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለው።

“ማል መሊሳ” አለበም በ iTunes በሀገራት ባለው ሽያጭ ያለው ደረጃ ሲታይ በአውስትራሊያ፣ በካናዳ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች 1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በአሜሪካ በ2ኛ ደረጃ ላይ፣ በብሪታንያ 9ኛ ደረጃ ላይ እንዲሁም በበርካታ ሀገራት እስከ 10 ባሉ ደረጃዎች ላይ መቀመጥ ችሏል።

በአይቱንስ ወርልድ የሙዚቃ ሽያጭ ሰንጠረዥ በየሰዓቱ የሚለዋወጥ ሲሆን ፤ የሙዚቃው የሽያጭ ደረጃ ሊጨምር አሊያም ሊቀንስ ይችላል።

አልበሙ በሀገር ውስጥ የኢንተርኔት የሙዚቃ መሸጫ በሆነው በ “ አውታር ” ላይም በ1ኛ ደረጃ እየተሸጠ ይገኛል ሲል አል አይን በድረገፁ ላይ አስነብቧል።

@tikvahethiopia