#ምርጫ2013

ኢትዮጵያ በ2 ዙር የምታደርገው 6ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያውን ዙር አጠናቃ የውጤት ይፋ መሆን እየተጠበቀ ነው።

ምርጫው ከፍተኛ የሆነ ቁጥር ያለው ዜጋ የተሳተፈበት መሆኑ መግለፁ ይታወሳል።

ዛሬ አውሮፓ ህብረት ፣ እንግሊዝና ጀርመን፣ ጃፓንን ጨምሮ 12 ሀገራት ምርጫውን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ምርጫውን ተዓማኒ ለማድረግ የተሻሻሉ ሕችን ማውጣትን ጨምሮ ምርጫ ቦርድ የወሰዳቸውን ርምጃዎች አድንቀዋል፡፡

ሲቪል ማኅበራት በምርጫው ሂደት ያሳዩት ጉልህ ተሳትፎ አመርቂ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ግን ፥ አንዳንድ ተቃዋሚዎች በታሰሩበት ፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ በተገደበበት፣ ጋዜጠኞች በሚዋከቡበት፣ የጸጥታ ችግር ባለበትና ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ምርጫ ዘመቻ ለማድረግ በተቸገሩበት ሁኔታ ውስጥ ምርጫው መካሄዱን የገለጡት ሀገራቱ፣ የሀገሪቱን ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ ንግግር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

አሜሪካም ከኢትዮጵያ ምርጫ ጋር በተያያዘ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል መግለጫ አውጥታለች።

አሜሪካ ምርጫው በአለመረጋጋትና ግጭት ውስጥ የተካሄደ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ነጻ እና ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ነው ብላለች።

አንዳንድ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸው እና ሌሎችም ራሳቸውን ከምርጫው ማግለላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ብሄራዊ መግባባት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል ብላለች።

በድኅረ-ምርጫ ለፖለቲካዊ ንግግር፣ ግጭቶችን ለመፍታትና ለብሄራዊ ዕርቅ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ ብላለች። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡና ተኩስ እንዲቆም ድጋሚ ጠይቃለች። #Wezema

@tikvahethiopia