የ40/60  መቶ በመቶ ከፋዮች ተፈረደላቸው።

40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መቶ በመቶ የከፈሉ ከ700 በላይ ተመዝጋቢዎች ተወሰነላቸው።

በቀድሞ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ/ም እጣ የወጣባቸው የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፣ መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ ቅድሚያ ለነሱ ሳይሰጥ እጣ መውጣቱን በመቃወም በፍርድ ቤት አሳግደው ነበር።

ሲከራከሩ ከርመው ዛሬ ሰኔ 16 ቀን 2013 ዓ.ም የታገደው ቤት እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tikvahethiopia