#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት እና በቀጣይ በሚሰጠው 2ኛ ዙር ክትባት መርሃ ግብር ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በህንድ ሃገር የተከሰተውን የኮቪድ-19 የወረርሺኝ መስፋፋት ተከትሎ በተለያዩ ሃገራት የክትባት እጥረት ማጋጠሙን በመግለጫቸው ላይ አስታውሰዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሀገራችንም #የክትባት_እጥረት ያጋጣመ ሲሆን ይህን እጥረት ለመፍታት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላቶች ጋር በመሆን ተጨማሪ ክትባቶችን ከለጋሽ አገሮችና እና ክትባትን ከሚያመርቱ ተቋማት ለማግኝት ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

እየተሰራ ባለው ስራ በቅርቡ በተለያየ መጠን ተጨማሪ ክትባት መምጣት እንደሚጀምር ከኮቫክስ የዓለም አቀፍ ጥምረት የተገለጸ መሆኑ ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብ መሰረት ሁለተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት የመጀመሪያ ዙር ለወሰዱ እና ክትባቱን ከወሰዱ ሶስት ወራት የሞላቸው የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች መስጠት እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

2ኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት እንደ መጀመርያው ዙር የክትባት አሰጣጥ መርሃ ግብር ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ይሰጣል ብለዋል።

መረጃው የጤና ሚኒስቴር ነው።

@tikvahethiopia