#Egypt

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ከግብጹ ፕሬዝዳንት ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ መነጋገራቸው ተሰምቷል።

ማክሰኞ ግብጽ የገቡት ልዑኩ ጄፍሪ ፌልትማን ትናንት ነው የግብጹን ፕሬዝዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲን ያነጋገሩት።

አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አሜሪካ በግድቡ ምክንያት ለተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማግኘት ውጤታማ ሚና እንድትጫወት ጠይቀዋል ተብሏል።

ግድቡ የሃገራቸው ህልውና ጉዳይ መሆኑን ተናግረው ግብጽ የውሃ ፍላጎቷን የሚጎዳን ማንንም እንደማትቀበል እንዳስታወቁ ተሰምቷል።

በተጨማሪ ፌልትማን የግብጹን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያነጋገሩ ሲሆን ፥ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ጥንቃቄ ለሚፈልገው ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ለመሻት ከልብ እንዳሰበበት ተናግረዋል።

ፌልትማን ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በቀጣይ እንደሚጎበኙ ዶቼ ቨለ አሶሼትድ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopiopia @tikvahethiopiaBOT