ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን 550 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን #ለኢዜአ አስታውቋል።

በተደረገው መከላከል 67 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።

አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 "መልካ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።

በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች ሞተዋል።

ምክንያት ?

አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

ምክንያት ?

ገና ፖሊስ እያጣራው ነው።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።

ምክንያት ?

የኤሌክትሪክ ኮንታክት ነው ተብሏል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።

ምክንያት ?

እስካሁን አልታወቀም።

#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT