#Axum

Save the Children ዛሬ በላከልን መግለጫ በአክሱም ከ3 ወራት ወዲህ የመጀመሪያ እርዳታ ማከፋፈሉን አሳውቆናል።

በዕርዳታው በከተማው የሚገኙ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው ምግብ፣ መጠለያና የንፅህና መጠበቂያዎችን እንዳገኙ ገልጿል።

አክሱም በቅርብ ጊዜ በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ በርካታ ተፈናቃዮችን ያስጠለለች ሲሆን ከ6 ሺህ የሚልቁ ተፈናቃዮች በተጣበቡ ትምህርት ቤቶች ፣ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችና በአከባቢው ነዋሪዎች ቤት ተጠልለው ይገኛሉ።

የSave the Children ልገሳ ለተፈናቃዮች መሰረታዊ የምግብ፣ መጠለያ እና ሌሎች አቅርቦቶችን ያካተተ ነው።

Save the Children በአክሱም በየካቲት መባቻ እጅግ አስፈላጊ ድጋፍ ማቅረብ ከጀመረ አንስቶ ለቀናት እህል ያልቀመሱና በሆስፒታሎች ባለው እጅግ ውስን የህክምና አቅርቦቶች የተነሳ አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶች ማግኘት ያልቻሉ ቤተሰቦችን አግኝተዋል።

ድርጅቱ በእስካሁኑ የምግብ እና ሌሎች እርዳታ ለ1,063 ቤተሰቦች ወይም 4,368 ሰዎችም መድረስ እንደቻለ ቢገልፅም አሁብም ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

* ከSave the Children የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ የያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia