#AxumUniversity

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂዎች የቲክቫህ አባላት እስካሁን አለመጠራታቸውን ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ እንደከተታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

ተማሪዎቹ በትግራይ ክልል ያለውን ከባድ ሁኔታ ቢረዱም ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰጠው አይነት መፍትሄ በፍጥነት ተግባራዊ ይደረጋል ብለው ቢጠብቁም እስካሁን ምንም እንደሌለ ገልፀዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ጉዳይ የሚከታተለው የሀገር አቀፍ ተማሪዎች ህብረት የአስክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች ጉዳይ ከዚህ በፊት ልክ እንደዓዲግራት መፍትሄ ያገኘ መሆኑን ገልጿል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጨርሰው በመውጣታቸው የዓዲግራት እንዲሁም የአክሱም ተማሪዎች መቐለ ገብተው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ በMoSHE አቅጣጫ ተቀምጧል።

በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተዋል።

ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገም።

ተማሪዎችን ለመጥራት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ በማስተባበር ላይ በመዘግየቱ ነው እስካሁን የቆየው።

ተመራቂ ተማሪዎችን ለመጥራት ስራዎች እየተሰሩ ፣ ዝግጅቶችም እየተደረጉ መሆኑን ተገልጿል።

በMoSHE አቅጣጫ መሰረት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጠናቀው የሚመረቁት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia