TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ደብረፅዮን መገለጫ ፦ ዛሬ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ ሰጥተው ነበር። ዶ/ር ደብረፅዮን እየተደረገ ባለው ጦርነት ኤርትራ ወታደሮች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥረው እየወጉን ነው ብለዋል። ይህን በተጨባጭ ማሳየት እንችላለን ፣ የያዝናቸው የኢሳያስ (ኤርትራ) ወታደሮች አሉ ሲሉ ገልፀዋል። እስካሁን ከ10 ሺ በላይ ወታደሮች ማርከናል ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የኢሳያስ ወታደሮች…
'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ'

ትላንት ምሽት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ' በአየር ተደብድቧል ፤ የትግራይ ክልል ከተሞች በጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በፌዴራል መንግስት ስር የሚተዳደረው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ" ተከዜ በቦንብ እንደተመታ የሚነገረው #ሀሰት ነው ብሏል።

ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው ነው ሲልም ገልጿል።

* የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በጉዳዩ ላይ ያወጣው መረጃ ከላይ ተያይዟል !

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia