#ATTENTION

ባለፉት 5 ወራት በኮሮና ቫይረስ የተያዙ #ወጣቶች ቁጥር በሶስት እጥፍ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት አሳውቋል። የዚህ ምክንያት አካላዊ ርቀትን መጠበቁ ላይ ችላ መባሉ እንደሆነ አስረድቷል።

ካለፈው የካቲት ወር መጨረሻ እስከ ሃምሌ ወር አጋማሽ በነበረው ጊዜ ከተመዘገቡት 6 ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ተጋላጮች ውስጥ 15 በመቶው ከ15-20 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ናቸው ተብሏል። ድርጅቱ እንደንፅፅር ከዚያ በፊት የነበረው 4.5 በመቶ ብቻ እንደነበር አንስቷል።

ወጣቶች ከሁሉም ሲነፃፀር አፍና አፍንጫ ማሸፈኛ ማድረግ ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ችላ የሚሉ መሆኑ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ስራ መሄድ ያለባቸው እነሱ፣ ወደ ባህር ዳርቻ ለማዝናናት የሚሄዱት እነሱ፣ ወደ መጠጥ ቤትም የሚሄዱት፣ ሱቅ የሚያዘወትሩትም እነሱ ናቸው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አሳስቧል።

ወጣቶች በብዛት በኮሮና ቫይረስ እየተያዙ ካሉባቸው ሀገራት መካከል አሜሪካ ፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጀርመን እና ጃፓን ይጠቀሳሉ።

የጃፓን ቶኪዮ ባለስልጣናት በከተማዋ የሚገኙ ወጣቶች በሚያዘወትሯቸው የመዝናኝ መንደሮች ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማካሄድ እቅድ ማውጣታቸውን ከቪኦኤ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia