#COVID19Ethiopia

- በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1 ሰው ከሸበዲኖ፣ 1 ሰው ከዳሌ፣ 1 ሰው ለዳራራ ፣ 1 ሰው ከአርቤጎና ነው።

- በኦሮሚያ ክልል 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ከሰበታ ፣ 1 ሰው ከሰንዳፋና 1 ሰው ከጉጂ ናቸው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ንክኪ ያላቸው ናቸው።

- በትግራይ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው።

- በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ከባህር ዳር ናቸው ፤ ሁለቱም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

- በአፋር ክልል 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 72 ደረሰዋል።

- በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- በሐረሪ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ግለሰቡ የሱማሌ ክልል ነዋሪ ሲሆን ለህክምና ሐረር መጥቶ ናሙና የተወሰደለት ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ባሉት ምስሎች ታገኛላችሁ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot