#Djibouti

በጅቡቲ በተደረገው 1,109 የላብራቶሪ ምርመራ ሁለት መቶ ሰማንያ (280) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 3,194 ደርሰዋል።

በተጨማሪ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ አጠቀላይ የሟቾች ቁጥር ሃያ ሁለት (22) ደርሷል።

በሌላ በኩል አርባ አምስት (45) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,286 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia