#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ሳቢያ 15 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ጠባቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ የፋይናንስ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ መናገራቸው DW ዘግቧል።

ሚኒስትሩ እንዳሉት በዚህ ሳቢያ በአገሪቱ ዕርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአጠቃላይ ወደ 30 ሚሊዮን ያሻቅባል።

መንግስት የኮሮና ወረሽኝን ለመከላከል ያቋቋመው የምኒስትሮች ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት ባደረገው እና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በመሩት ውይይት ለዚህ ብቻ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ገልጸዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን ለመቋቋም ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከአውሮፓ ኅብረት፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ብሪታኒያ እና ቻይና 2.1 ቢሊዮን ዶላር ዕገዛ መጠየቋን አቶ አሕመድ ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር በቅርቡ ለኢትዮጵያ ሊሰጥ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በትናንትናው ዕለት የዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ጫና ለመቋቋም የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ የ411 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ አጽድቋል። የዓለም ባንክ በበኩሉ 750 ሚሊዮን ዶላር የበጀት ድጋፍ ሊሰጥ እንደሚችል የፋይናንስ ሚኒስትሩ አስረድተዋል - #DW

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia