#EPHI

ኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከመጋቢት 03 ቀን 2012 ዓ.ም ይፋ ከተደረገበት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በኮሮና ቫይረስ መታመማቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 2,516 ሰዎች ተለይተዋል ሲል የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ገለጸ።

ከእነዚህ መካከል 1,953 ሰዎች ክትትላቸውን አጠናቅቀው ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆን፣ 521 ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛሉ ብሏል።

በሀገራችን እስካሁን በቫይረሱ መታመማቸው ከተረጋገጡ ሰዎች ውስጥ 42ቱ (31%) የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ሰዎች መሆናቸው ተረጋግጧል ሲል ገልጿል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia