"ጦርነቱን አሸንፈናል!" - ጠ/ሚ ጃሲንዳ አርደን

ኒውዚላንድ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን መዛመት ለከለላከል ስትል ደንግጋው የነበረውን የመንቀሳቀስ ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ አንስታለች፤ ሀገሪቷ አዲስ ምዕራፍ ላይ መድረሷንም አስታውቃለች። አንዳንድ ትምህርት ቤቶችና የንግድ ተቋሞች እንዲከፈቱ ተፈቅዳል።

የኒውዝላንዷ ጠ/ሚ ጀሲንዳ አርደን - "አሁን በኒውዚላንድ ውስጥ ያልተለየና የተስፋፋ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት በማህበረሰቡ ውስጥ የለም ፤ ይህን ጦርነትም አሸንፈናል" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይህ ወረሽኝ [ኮቪድ-19] መቼ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠፋ እንደማይታወቅ በማስገንዘብ ፤ የሰዎች ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት መደበኛነት እንዲመለስ የሚያስችል የተረጋገጠ ሁኔታ እንደሌለም አስጠንቅቀዋል።

"ሁሉም ሰው ወደ ቀደመው እና ወደናፈቀው የማህበራዊ ግንኙነት መመለስ ይፈልጋል ፤ ይህን በሙሉ መተማመን ለማድረግ ግን በከፍተኛ ጥንቃቄ ቀስ በቀስ መንቀሳቀስ አለብን" ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት አዲስ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ አንድ (1) ብቻ መሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። በአጠቃላይ 1,469 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህም ውስጥ 1,180 ሰዎች አገግመዋል፤ በሀገሪቱ የሞቱት 19 ሰዎች ናቸው።

ኒውዚላንድ ውስጥ ለአንድ ወር ያክል ሰዎች ከቤታቸው እንዳይወጡና አስፈላጊ ያልሆኑት የንግድ ተቋማት ሁሉ ተዘግተው ነበር።

#VOA #AlJazeera
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia