ኢትዮጵያ ብቻዋን ነፃ አትሆንም!

(ዶክተር - TMES)

ከሰሞኑን በኢትዮጵያ ሪፖርት እየተደረጉ ያሉት ኬዞች ማነስ በርካቶችን እያዘናጋ እንደሆነ እየታየ ነው።

መልካም ዜናን የሚጠላ የለም ግን እውነታው ይህ አሁን ድረስ ፈውስ ያልተገኘለት በሽታ በመላው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑ ነው።

ዶክተር ፅዮን ፍሬው ከኒው ዮርክ እንዳሉት በየቀኑ የሚመዘገበው ቁጥር 0 እና 1 ሆነ ማለት የኮሮና ቫይረስ እየጠፋ ነው ማለት አይደለም።

የፋሲካ ሰሞን በሀገራችን የነበረው መዘናጋትና ቸልተኝነት እየባሰበት እንጂ እየቀነሰ አልመጣም። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

ሁላችንም በየእምነታችን ይህ በሽታ ከዓለም እንዲጠፋ፤ ፈጣሪም ለዚህ ወረርሽኝ መፍትሄ ለማምጣት የሚሰሩትን ሳይንቲስቶን መንገዱን ያሳያቸው ዘንድ እየተማፀንን በከፍተኛ ደረጃ ጥንቀቄያችን እናጠንክር።

ኢትዮጵያ ብቻዋን በፍፁም ነፃ አትሆንም ፤ ጎረቤት ሀገራት በወረርሽኙ እየታመሱ እኛ ጤና ሆነን እንኖራለን ማለት አይቻልም ፤ አይደለም ጎረቤት ሀገራት የቻይና፣ አሜሪካ፣ ኢራን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ጣልያን ...ሌሎችም ሀገራት ህዝቦች ጤና መሆን ካልቻሉ ህይወታችን እንደተቃወሰ ይቀጥላል፤ ምክንያቱም ተሳስረናልና!

ዘወትር ለኢትዮጵያ #ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጤና መሆን፣ ለሰው ልጅ መዳን፣ ለሰው ልጅ ሰላም መሆን በየእምነታችን ፈጣሪን እንለምን።

እኛ የጤና ባለሞያዎች ደከመን ሰለቸን ሳንል ይኸው ህይወታችን ሰጥተን እያገለገልን ነው፤ እናንተም በመዘናጋት የሚመጣውን የከፋ ቀውስ ለመከላከል አብራችሁን ቁሙ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia