(በተሾመ ሃይሉ)

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በአካባቢው ለሚገኙና ዝቅተኛ የሆነ ገቢ ላላቸው ከ170 በላይ ነዋሪዎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለአንድ ወር የሚሆን የምግብ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርስቲው በሚገኝበት ሐረማያ ከተማ ባቴ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑና በቀን ስራና በሌሎች አነስተኛ ስራዎች ተሰማርተው ለሚኖሩ ዝቅተኛ በሆነ ገቢ ለሚተዳደሩና በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ 178 ነዋሪዎች ነው የምግብ ድጋፉ የተደረገው።

ድጋፍ ለተደረገላቸው ለእያንዳንዳቸው ለአንድ ውር ሊሆን የሚችል ቀለብ ሲሆን በዚህም 15 ኪሎ ጤፍ፣ 40 ኪሎ በቆሎ፣ 20 ኪሎ ማሽላ፣ 25 ኪሎ ማካሮኒ፣ ማሽላ፣ ቦሎቄ፣ የምግብ ዘይትና ሌሎች አልሚ ምግቦችና የንፅህና መጠበቂያ ተሰጥቷቸዋል።

በአጠቃላይ በተሰጠው የምግብ ድጋፍ ለእያንዳንዳቸው ከ3 ሺህ ብር በላይ ሲሆን በአጠበቃላይ 688 ሺህ 860 ብር ወጪ እንደተደረገበት የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ የገለፁ ሲሆን አሁን የተደረገው የምግብ ድጋፍ የመጀመሪያው ዙር እንደሆነና ቀጣይነት እንደሚኖረው አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia