"በክትባት ፍለጋው ላይ ዓለም አቀፍ ርብርብ ሊደረግ ይገባል" - አንቶኒዮ ጉተሬዝ (የተመድ ዋና ፀሃፊ)

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ክትባት ፍለጋው ላይ በሚደረግ ጥረት አለማቀፍ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

«በመላው ዓለም መንግሥታት በአንድ በኩል ኢኮኖሚያቸውን ከውድቀት ለመታደግ ብርቱ ትግል ያደርጋሉ ፤ በሌላ በኩል በወረርሽኙ የተጠቁ ሰዎች ከ2,8 ሚሊዮን በላይ ሆነው ብርቱ ፈተና ከፊት ተጋርጧል» ብሏል ድርጅቱ።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በፍጥነት መዛመት ክትባት ፍለጋው ላይ የሚደረገው ጥረትም የዚያኑ ያህል ፈጣን ካልሆነ ዋጋ ሊያስከፍል እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አስጠንቅቀዋል። በክትባት ፍለጋው ላይ ዓለም አቀፍ ርብርብ ሊደረግበት ይገባልም ብለዋል።

እስካሁን እየተደረጉ የነበሩ ጥረቶች ከተስፋ የዘለለ ተጨባጭ ውጤት አልተገኘም ያሉት ዋና ጸሐፊው ምናልባትም ረዘም ያለ ጊዜ ሊጠይቅ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

'ከእስከ ዛሬው ሁሉ የሰው ልጅ የተለየ ጠላት ነው የገጠመው' ያሉት አንቶኒዮ ጉተሬዝ ክትባቱን ለማግኘት በሚደረግ ጥረት የአለም መሪዎች ከግሉ ዘርፍ ጋር በመቀናጀት መስራት ይጠበቅባቸዋል በማለት አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia