#Telegram

የቴሌግራም ወርሃዊ ተጠቃሚዎች ቁጥር 400,000,000 መድረሱን ድርጅቱ አስታውቋል። በቅርቡ አሁን ባለው አገልግሎት ላይ ተጨማሪ ይዘቶችንም እንደሚያካት ይጠበቃል። ድርጅቱ በ2022 1 ቢሊዮን ተጠቃሚዎች እንዲኖሩት እየሰራ ነው።

በነገራችን ላይ በኢትዮጵያም የቴሌግራም ተጠቃሚ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው። ከፍተኛ ተጠቃሚ ካለባቸው ሀገራትም አንዷ እንደሆነች ይነገርላታል፤ በሀገሪቱ ምን ያህል ተጠቃሚ እንዳለ የሚያሳይ አሁናዊ ማስረጃ ባይኖርም።

ከዚህ ቀደም በቴሌግራም ላይ እንቅስቃሴ የማያደርጉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ሚዲያዎች ፣ ታዋቂ ሰዎችም በስፋት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

አሁን ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባመጣው ችግር ምክንያት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን በቴሌግራም እያስተማሩ እንደሆነም እየሰማን ነው።

ለመሆኑ ይህን ያህል ለምን ተወደደ ?

- ከምንም በላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

- ብዙ ወጪ አያስወጣም፤ በቀላሉ አገልግሎት ይሰጣል። ኔትዎርክ ደካማ በሆነባቸው ቦታዎች ላይም ለመጠቀም አያስቸግርም።

- ማንም ሰው የፈለገው ብቻ መልዕክት ነው የሚደርሰው ፤ ያለፍላጎቱ ምንም መልዕክት እንዳይደረሰው ማድረግ ይችላል።

- ተጠቃሚዎች እርስ በእርስ የሚሰዳደቡበት ዕድል እጅግ በጣም አነስተኛ ነው ፤ ፈልገው ወደ ግሩፖች እና ቻናሎች ካልገቡ በስተቀር።

- የምልዕክት ልውውጥ ቀልጣፋ ነው። በአነስተኛ ገንዘብ የፈለግነውን ፋይሎችን ለመላላክ አመቺ ነው።

ሌሎችም በተጠቃሚዎች በኩል የሚሰጡ ምክንያቶች ብዙ ናቸው!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) ቴሌግራምን ብቸኛው የመልዕክት መለዋወጫ አድርጎ መስራት ከጀመረ ሃምሌ 19/2012 ዓ/ም ሶስተኛ ዓመቱን ይይዛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia