#CHINA

በቻይና ያሉ ተማሪዎችና ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መከላከያ የሚውል 452 ሺህ 589 ዩዋን ድጋፍ መደረጉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

በቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎችና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉ የቤጅንግ ነዋሪ በድምሩ 101 ሺህ 189 ዩዋን ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

በሌላ በኩል በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች 9 ሺህ 500 ዩዋን ፣ ከተለያዩ የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አባላት ማለትም ከጓንዦ 3 ሺህ ዩዋን ፣ ከሻንሃይ 5 ሺህ 200 ዩዋን ፣ ከክችንችን 211 ሺህ ዩዋን ሲሰበሰብ በጓንዦ ከተማ ዳያስፖራ አባላት ደግሞ 120 ሺህ ዩዋን ድጋፍ ተገኝቷል።

ከዚህም ውስጥ 351 ሺህ 400 ዩዋን በቀጥታ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኢትዮጵያ ለተቋቋመው ብሔራዊ ሀብት አሰባሳቢ ግብረ ኃይል መላኩን ኤምባሲው ገልጿል።

ቀሪው ከተማሪዎች እና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉት የቤጂነግ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ የተገኘው 101 ሺህ 189 ዩዋን ደግሞ የህክምና መሳሪያዎችን ገዝቶ ለመላክ ምርቶችን በማፈላለግ ላይ መሆኑን ኤምሳቢው አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia