የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልል!

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በ22 ዋና ዋና ጉዳች ላይ ከመከረ በኋላ ሶስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል አስታውቀዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ ፣ ከከተማ ወደ ገጠር፣ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ዝውውሮች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ታግደዋል፡፡ ህዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎችም እንዳይካሄዱ መታገዳቸውንም ዶ/ር ደብረጽዮን ገልፀዋል፡፡

እንደ ሠርግና ተስካር ያሉ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችም ለጊዜው እንዳይካሄዱ የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት የተላሉፉት ውሳኔዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ተግባራዊ እንሚደረጉና በሽታው ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተገመገመ የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ መናገራቸውን የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia