ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ከውይይቱ በኋላ የሚከተሉት ዐበይት እርምጃዎች የሚተገበሩ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፦

- ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን አንስቶ፣ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎችን የሚያስቆምና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስተገብር ይሆናል፡፡

- የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የመንግስት ተቋማት ማህበራዊ ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግና ስብሰባ ሲያካሄዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው፡፡

- የመንግስት ተቋማት የተቀጣሪዎቻቸውን ሁኔታ በማጣራት እንደየሁኔታው አንዳንዶች በቤታቸውን ሆነው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

- የሕዝብ መጓጓዠ አገልግሎት ሰጪዎች አጨናንቆ ተሳፋሪዎችን መጫን የማይችሉ ሲሆን፣ ይህን ማድረጋቸው በትራፊክ ፖሊስና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግበት ይሆናል፡፡

- ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊትና ፖሊስ ውስጣዊ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ በአገር ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የመከላከል ስራን ለማስፈጸም ማዘጋጀት፣

- በተጠቃሚው ማህበረሰብ ላይ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

- መገናኛ ብዙሃን በትኩረት በየደረጃው ግንዛቤን የማሳደግ ሚናን መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡

- ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት በድንበር አከባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታሉ፡፡ ይህ እርምጃ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦችና አስፈላጊ መገልገያዎችን አይጨምርም፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia