#ETHIOPIA

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ [face mask] የሚከተሉት ሰዎች እንዲጠቀሙት ይመከራል፦

- የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

- ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ስያስለን ወይም ስያስነጠሰን፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

- የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ስሆን ብቻ ነው፡፡ ህብረተሰቡ መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ጤናሚኒስቴር #ፋናብሮድካሲንግ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia