This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• መልአከ ህይወት ቆሞስ አክሊለ ማርያም የአገልግሎት ስፍራቸው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንዳፋ በኬ ማርያም መሆኑን ይናገራሉ በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኝ መስጂድንና ቤተ ክርስቲያንንም በእኩል ቆመው ያሳንጻሉ። መልዕክታቸውን እንዲህ አስተላልፈዋል፡-

- ኢትዮጵያዊያን ድሮ የሚያስቡት ሰውን ሰው በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ያለው ነገር እንኳን በተማሩት በእኔ ባልተማርኩት፣ በኔ በታናሹ፣ በኔ በመነኩሴው ዘንድ ያሳስበኛል፡፡

- ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል ለትምህርት ሄደው የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ያሳስበኛል፡፡ እኔ ያደኩት አሁንም ያለውት በኦሮሚያ ክልል ነው በእውነት የኦሮሞ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው። ይህንን ስራ የሚሰሩት የፓለቲካ ትርፍ ያላቸው ናቸው፡፡

- እኔ በየዕለቱ ቅዱስ ቁርዓን አነባለሁ ቅዱስ ቁርዓን ማንበብ ከጀመርኩ በኀላ ኢትዮጵያ ብዙ እሴት ያላት ሀገር መሆኗን ነው የተረዳውት፡፡

- በአሁን ሰዓት በእምነት መኖር ሳይሆን በእምነት መሸጋገር ያስፈልጋል፡፡

🎧 11 MB [WiFi ተጠቀሙ]

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia