ምክር ቤቱ የጥላቻ ንግግር እና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መራ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ካነሱ በኋላ ነው ምክር ቤቱ ረቂቁን ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ የመራው።

በሃሰተኛ መረጃዎች የተነሳ በሃገሪቱ የሰው ህይወት ሲጠፋ እና ንብረትም ሲወድም የሚስተዋል ነው። በመሆኑም ይህ ረቂቅ አዋጅ የጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን በህግ መከልከል አስፈላጊ በመሆኑ ነው የወጣው ተብሏል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-26

(EBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot