ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አሃዱ ቲቪ ሎጎዬን ተጠቅሞ ሀሰተኛ መረጃ አቅርቧል፤ ድርጊቱ ተገቢ ስላልሆነ ሊቆም ይገባል ብሏል!

"የአሃዱ ቲቪ መማርና ማስተማር ያልጀመሩ ብሎ በዜና ላይ ከጠቀሳቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን ሎጎ በመለጠፍ የሃሰት ዜና በቀን 10/03/2012 ዓ.ም በምሽት 2፡00 ሰዓት ዜና ላይ አሰራጭቷል። ይህ ደርጊት ተገቢ ስላልሆነ ሊቆም ይገባል።" - ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ

መረጃውን የተከታተሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቡሌ ሆራ ቤተሰቦችም የተሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ ነው፤ ይህን መሰል ድርጊቶች ወላጆችን ስለሚረብሽ ሊታረም ይገባዋል፤ ጣቢያው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል ብለዋል። እስካሁን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ችግር አልገጠመንም የመማር ማስተማር ስራውም አልተቋረጠም በሰላም እና በፍቅር እየተማርን እንገኛለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia