#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ የነበረው የኢሬቻ በአል አከባበር ባማረ መልኩና በሰላም ተጠናቋል። ይህን አስመልክቶም የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለከተማዋ ነዋሪዎችና ለበአሉ አከባበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሁሉ የምስጋና መልእክት አስተላልፈዋል።

ኢንጂነር ታከለ በሁሉም የከተማዋ ጫፎች የሚገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ያሳዩት ትብብር የሚደነቅና የሚከበር ነው ብለዋል። በአሉን ለማክበር ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡትን በልዩ ፍቅርና ያላቸውን በማቅረብም ጭምር አክብሮታቸውን ስላሳዩም ለከተማዋ ነዋሪዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የከተማዋ ባለሀብቶችም የበአሉን አከባበር በመደገፍ በአሉ እውን እንዲሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናን አቅርበዋል። በበአሉ ላይ አንድም የጸጥታ ችግር እንዳይፈጠር በበቂ ዝግጅትና በሀላፊነት ስሜት በብቃት ለሰሩ የጸጥታ አካላትም ምስጋናን አቅርበዋል።

ለጸጥታው መከበር ወጣቶች ያሳዩትንም ተሳትፎና ትብብርም የሚደነቅ ነው ብለዋል ኢ/ር ታከለ ኡማ። ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአጠቃላይም አዲስ አበባ ህብረብሄራዊነቷን በጠበቀና ባማረ መልኩ የኢሬቻ በአል በመዲናዋ እንዲከበር ድጋፍ ላደረጉና በጨዋነት ለተባበሩ በሙሉ ከፍ ያለ ምስጋናቸውን መግለፃቸውን የከንቲባ ፅሀፈት ቤት አስታውቋል።

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia