አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪትን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በነሃሴ ወር መጠናቀቂያ ላይ ነበር ያፀደቀው። አዲሱ መመሪያ ከፈቀዳቸው አሰራሮች መካከል በኮድ 1 ታክሲ መመዝገብ የሚቻሉ ባለ ቢጫ ወይም ባለሰማያዊ ቀለም ታክሲዎች ሊሆኑ እንደሚችሉና ቴክኖሎጂ አግዟቸው በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ ታክሲዎች ሆነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው የኢኮኖሚክ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ለሸገር ራድዮ በሰጡት ማብራሪያ ከዚህ ወዲያ ለሚተገበረው መመሪያ ይህን ብለዋል፦

"የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት የሚባል መመሪያ ወጥታል። የወጣው መመሪያ ከዚህ በፊት መጠቀም ሚችሉም ናይችሉም የሚለያይ ነበረ አሁን ግን ማንም ሰው መጠቀም የሚችልበት ከዚህ በፊት አግደን የነበረው አገልግሎት ክፍት ያደረግንበት መመሪያ ነው። ከዚህ በፊት ተከልክለው የነበሩ አገልግሎቶች ክፍት ያደረገ አዲስ መመሪያ ነው። ...ከዚህ በፊት ኮድ 1 ታክሲ መስጠት ተከልክሎ ነበር ስለዚህ ይህ መመሪያ ኮድ ኣንድ ታክሲ ማውጣት እንዲቻል ፈቅዶ የወጣ መመሪያ ነው። ማንም ሰው ሄዶ ኮድ 1 ታክሲ አውጥቶ...ሰማያዊና ነጭ ቀለም ሊሆን ይችላል ቀብቶ መንቀሳቀስ እንዲችል የፈቀድንበት ነው። ስንፈቅድ ግን ወደ ኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት ሲስተም ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው። ወደዛ ከገቡ ገብተው ለመስራት ፍቃደኛ ከሆኑ በስልክ ጥሪ፣ ማስተናገድ ፍቃደኛ ከሆኑ ይሄ ተከልክሎ የነበረውን የሚፈቅድ መመሪያ ነው።"

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-4