#ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ አባይ በሚባል መድኃኒት ቤት ውስጥ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወሩ የነበሩ መድሃኒቶችን ይዟል።

መድሃኒቶቹ 27 ሺህ 470 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ሲሆን፥ የመድኃኒት ቤቱ ባለቤት በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የቁጥጥሩ ባለቤት በመሆን ከማንኛውም ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ራሱን በመጠበቅ የቁጥጥር ስራውን እዲያግዝም ጥሪውን አቅርቧል።

መሰል ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ድርጊቶች ሲፈጸሙ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር በ8482 ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፍትህ አካላትና የጤና ተቆጣጣሪዎች እንዲጠቁም ጠይቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia