የኢትዮ- አሜሪካ ዶክተሮች ቡድን ለኢትዮጵያ ስፖርተኞች የቀዶ ህክምና አገልግሎቴን እየሰጠሁ ነው ብሏል:: የኢትዮ- አሜሪካ ዶክተሮች ቡድን አባላት ለእግር ኳስ ተጫዋቾች እና ሌሎች ያለምንም ክፍያ የቀዶ ህክምና አገልግሎት በአቤት ሆሰስፒታል (AaBET) እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ዶክተሮቹ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ #በነፃ የ15 የአጥንት ህሙማንን ቀዶ ጥገና የከወኑ መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አቤት ሆስፒታል ውስጥ ወደ 200 የሚጠጉ ህሙማን የአጥንት ቀዶ ጥገናውን የሚጠብቁ ሲሆን ለህክምናው እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 200 ሺ ብር ይጠየቃል ተብሏል፡፡ የኢትዮ- አሜሪካ ዶክተሮች ቡድን አባላት በአጥንት ቀዶ ጥገና ባለሙያው ዶ/ር ክብረት ከበደ እየተመሩ አገልግሎቱን እየሰጡ ነው፡፡

የህክምና ቡድኑ የአጥንት ጡንቻ መዛባት ያለባቸውን ኢትዮጵያውያን የስፖርት ሰዎችን ደርሸላቸዋለሁም ብሏል፡፡ በተጨማሪም በዘርፉ ታዋቂ ባለሙያዎችን ማካተቱንም አስታውቋል፡፡ ቡድኑ አባላቱን ለማገዝ የህክምና መሳሪያዎችን እና ባለሙያዎች አቀናጅቶ ይዞ እንደመጣ ገልጧል፡፡ ከመጡት መሳሪያዎች ውስጥ አቤት ሆስፒታል ውስጥ መትከሉን ተናጋሯል፡፡

የኢትዮ- አሜሪካ ዶክተሮች ቡድን ከ340 በላይ አባላትን የያዘ ሲሆን በየዓመቱ ያልተቋረጠ የህክምናና እና ቀዶ ጥገና ትምህርቶችን ለሀገር ቤት የህክምና አባላት ከመስጠቱ በተጨማሪ በ110 ሚሊዬን ዶላር በጀት ዓለም አቀፍ ቴሪሸሪ ሆስፒታል እያስገነባ መሆኑን እወቁልኝ ብሏል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia