#አሳዛኝ_ዜና

በጅማ ዞን ኦሞናዳ ወረዳ በጊቤ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ባህላዊ ጀልባ መስጠሟ ተሰማ። ከጣውላ የተሰራችው ጀልባ ከቀኑ 5 ስአት ከ30 አካባቢ ወደ አሰንዳቦ ገበያ የሚመጡ 18 ሰዎችን አሳፍራ በመጓዝ ላይ እያለች ተሰብራ መስጠሟን ነው የወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ ከሊፋ የተናገሩት። አደጋው እንደተከሰተም የወረዳው አስተዳደር አካላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ጠላቂ ዋናተኞች ደርሰው የ13 ሰዎችን ህይወት ማትረፍ ተችሏል ብለዋል።

ቀሪዎቹ 5 ሰዎች ግን እስካሁን አልተገኙም፤ ፍለጋውም መቀጠሉ ነው የተነገረው።የጀልባዋ ቀዛፊም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። አደጋው የደረሰባቸው የጀልባዋ ተሳፋሪዎች ከሰኮሩ እና ኦሞናዳ ወረዳ ወደ አሰንዳቦ ገበያ ሲያመሩ የነበሩ ናቸው የተባለ ሲሆን÷ ህብረተሰቡ ደህንነታቸው አስጊ በሆኑ ጀልባዎች ከመጓዝ በመቆጠብ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia