#ሐዋሳ ተቃውሞ እና ግጭት!

የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ለዛሬ ለማወጅ መቀጠሩን ተከትሎ በሐዋሳ እና አካባቢዋ ግጭት ተቃውሞ ተከስቷል። የጥያቄ አራማጆች ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ እንደገለፁት የሲዳማ ሽማግሌዎች እና ወጣት የጉዳዩ አቀንቃኞች ዛሬ ጠዋት ሊያካሂዱት ያቀዱት ስብሰባ አካባቢውን በዘጉት በፀጥታ ኃይሎች ተደናቅፏል። ባለሥልጣናት ወደዚያ ባለመምጣታቸው፤ እና ወደ መሰብሰቢያው ስፍራም እንዳያልፉ ያገዷቸው የፀጥታ ኃይሎች ላይ ወጣቶቹ ድንጋይ መወርወራቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

ሐዋሳ ከተማ ላይ በቁጣ ወደ ጎዳና የወጡት ዜጎች ጎማ በማቃጠል ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭትም ቢያንስ የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱን ሌሎች ደግሞ መጎዳታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶይቼ ቬለ ገልጸዋል።

የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ሳርሚሶ ጭንቅላቱን በጥይት መመታቱ የተገለፀው ተጎጂ ወደ ሐኪም ቤት ከሄደ በኋላ ሕይወቱን ማጣቱን ለጀርመን ራውዮ ዘጋቢ ገልጸዋል።

«መጀመሪያ ላይ ትንሽ ጭንቅላቱ ላይ የቆሰለ ሰው ገብቷል። እሱ የመጀመሪያ ርዳታ ሰጥተን ወደ ቤቱ ሄዷል። ከዚያ ቀጥሎም ደግሞ አንድ ሴት ነበረች የመጣችው። ባጠቃላይ አራት ወንድ እና አንድ ሴት ነበር የመጡት። አንደኛው ከአዳሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመጣ ከዚያ ሪፈር የተደረገ ሰው ነበረ ጭንቅላቱ ላይ ነበር ቆስሎ የነበረው፤ ቁስሉ አሁን ሀኪሞች እንዳረጋገጡት በጥይት የተመታ ይመስላል። ከፍተኛ የሆነ ቁስል ነው። እሱ አዳሬም ወደ እኛ እንደላከ እኛ ጋርም ብዙ ሳይቆይ ሊያርፍ ችሏል።» ሌሎቹ ተጎጂዎችን በተመለከተ የሚታየው እስካሁን ለከፋ አደጋ የሚያደርስ እንዳልሆነም አክለው ገልጸዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia