#NewsAlert የኤሌክትሪክ ኃይል ለማግኘት የነበረው ፈረቃ ከዛሬ ጀምሮ እንደማይኖር ታውቋል፡፡ በበጋና የበልግ ወቅቶች በቂ ዝናብ ባለመጣሉ የኢትዮጵያ የኤሌክተሪክ ኃይል ማመንጫ አንዳንድ ግድቦች የውኃ እጥረት አጋጥሟቸው እንደነበርና የኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011ዓ.ም በፈረቃ እንዲሆን መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ በተገኘው መረጃ መሠረትም ከዚህ በፊት በተሰጠው መግለጫ መሠረት ምንም እንኳ ግድቦች በቂ ውኃ ባይዙም በክረምቱ እንደሚሞሉ ታሳቢ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ፈረቃው እንዲቀር ተደርጓል፡፡

የኢፌዴሪ ውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለ ግንቦት 09 ቀን 2011ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ከግንቦት 01 ቀን ጀምሮ በውኃ እጥረት ምክንያት ወደ ፈረቃ መገባቱንና ፈረቃው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ሊቀጥል እንደሚችል ተናግረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዝርዝር መግለጫ ከቀኑ 9፡00 ላይ ለመስጠት የመገናኛ ብዙኃንን ጠርቷል።

Via #AMMA/#አብመድ/
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia