"ክልል የመሆን ጥንያቄ ህገ መንግስታዊ መብት ነው። ማንም ህዝብ ክልል ልሁን ብሎ መጠየቅና በህግ አግባብ ጉዳዩን ማስፈፀም መብቱ ነውና አትችልም መጠየቅ አንለውም፤ ህገ መንግስትን መብቱ ነውን ይሄን ህገ መንግስታዊ መብት ህጋዊ የሆነውን ጥያቄ በህጋዊ መንገድ ብቻ ነው መልስ ማግኘት የሚችለው።

ህጋዊ ጥያቄን በግርግር ከፈለክ ዘላቂ መፍትሄ አታመጣም፤ ፍትህ እንኳን ብታመጣ ርትዕ አታመጣም። ፍትህም ርትዕም Equally exercise ለማድረግ ከፈለገ አንድ ማህበረሰብ በህግ የጠየቀውን በህግ እስኪመለስ መጠበቅ ያስፈልጋል። ምን ማለት ነው፤ አንድ ክልል እራሱን በራሱ ማስተዳደር ሲፈልግ ያንን ጉዳይ የሚያስፈፅመው የምርጫ ቦርድ ነው።...ይሄ ተቋም በሁለት እግሩ ሳይቆም ክልል የመፍጠር ጉዳይ ብንሞክር ግን ፍላጎት ብቻ ነው የሚሆነው።

...አሁን ደቡብ አካባቢ ያለውን ነገር መንግስት በክብር ተቀብሏል። ደኢህዴን የሚባለው ክልሉን የሚያስተዳድረው ድርጅትም ጥያቄውን ተቀብሎ በህግ እየመረመረ ይገኛል። ደኢህዴን የመጨረሻ ውጤቱን እስከሚያሳውቅ፤ምርጫ ቦርድ ዝግጅቱን እስከሚያሳውቅ በደቡብ ክልል ውስጥ ክልል ለመሆን የጠየቃችሁ ህዝቦች በከፍተኛ ትዕግስት እንድትጠብቁን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

ከህጋዊ መንገድ ውጪ ምንም አይነት ሙከራ ማድረግ ሱማሌ እንደሆነው ደቡብም ይሆናል፤ በኢትዮጵያ አንድነት የሚደራደር መንግስት የለም። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ተቀብለናል #በትዕግስት መጠበቅ! አልተቀበልንም ሲባል በህጋዊ መንገድ እናስተካክለዋለን። በዚህ መንገድ ቢታይ ጥሩ ነው በደቦ፣ በጩኸት የሚፈጠር ነገር ከእንግዲህ በኃላ ማስተናገድ ትዕግስታችን አልቋል። ሁሉም ስርዓትን ጠብቆ ይሄዳል፤ በስርዓት እንመልሳለን ያን የማይጠብቅ ከሆነ በተለመደው መንገድ እናስተካክለዋለን!" ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ~#ቲክቫህ