#update ያሬድ ዘሪሁንን ጨምሮ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የቀድሞ ሃላፊዎችና ሠራተኞች በዐቃቤ ሕግ የቀረቡባቸው ምስክሮች ቃል ውድቅ እንዲያደርግላቸው ችሎቱን ጠይቀው ተቀባይነት አላገኙም፡፡ ተከሳሾቹ ዐቃቤ ሕግ የምስክሮች ጥበቃ አዋጅን ያላግባብ ስራ ላይ አውሏል፤ ለምስክሮች ጥያቄ እንዳናቀርብ ታግደናል፤ የቀድሞ ተቋማችን ባልደረቦች ከሕግ ውጭ በእኛ ላይ ምስክርነት መስጠታቸው ስህተት ነው ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ ችሎቱ ግን አቤቱታው በይግባኝ ለመቅረብ የሚገባው አይደለም በማለት ጉዳዩን እንደዘጋው ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በፌስቡክ ገጹ አስፍሯል፡፡

Via #wazema/የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ/
🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia