"ትላንት በቃሊቲ #አብዱልቃድር_መስጂድ የተፈጠረው ችግር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዕውቅና ውጪ የተደረገ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ጥያቄ ቢኖር በመነጋገር መፍታት እየተቻለ አላስፈላጊ #ጉዳት ወደሚያደርስ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባት ከየትኛውም አካል የማይጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳዩ #ከዕውቅናው_ውጪ እንዴት እንደተፈፀመ እና በቀጣይም መጣራት የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ በመፈተሽ በመዋቅሩ የማስተካከያ ዕርምት እንደሚወስድ በዚህ አጋጣሚ ያረጋግጣል፡፡ በተፈፀመው ነገር ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ የተሰማውን #ሃዘን ይገልፃል፡፡" Mayor Office of Addis Ababa

@tsegabwolde @tikvahethiopia