#update ሦስት የተቀዋሚ ድርጅት አመራሮች ወደ በርሊን አቅንተው ከጀርመን ቡንድስታግ (ፓርላማ) ጋር ተነጋግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር በትዊተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ከአርበኞች ግንቦት 7 ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ከኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግሬስ መረራ ጉዲና (ዶ/ር)፣ ከኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ሌንጮ ለታ በጉብኝቱ ተካፋይ ሆነዋል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሽታየ ምናለ እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳም ተገኝተዋል፡፡ ከቡድኑ ጋር የተመካከሩት የቡንድስታጉ ምክትል አፈ ጉባዔ ክላውዲያ ሩዝ ሲሆኑ ለቡድኑ ስለ ጀርመን ፖለቲካ ፓርቲዎች አደረጃጀትና ምርጫ ሕግጋት ገለጻ ተደርጎለታል፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia