#update የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ተደረገ፡፡ ግምገማው የተካሄደው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ነው፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት በድረገጹ እንዳስነበበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለከተም የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዳቀረቡት የሲቪል ምሕንድስና ሥራው ሰማንያ ሦስት በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው ሃያ አምስት በመቶ፣ የብረታ ብረት ሥራው አሥራ ሦስት በመቶ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ክንዋኔ ስልሳ ስድስት በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia