ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ🔝

ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲንና ልዑካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ስለማስጠበቅና በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነቶች ላይ ደርሰዋል።

ፕሬዝዳንት ሙሴ በበኩላቸው ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለቀጣናው ውሕደት የወሰዷቸውን ርምጃዎች በማንሣት አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይብልጥ ተቀራርቦ አብረው እንዲሠሩ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል። በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ ተስማምተዋል። ሲያጠቀልሉም ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥር ላይ ተወያይተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia