ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት ወንጀለኞችን ለፍርድ ስለማቅረብ በተመለከተ ለተነሱት ጥያቄ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀል ሰርቶ ያልታሰረ ሰው የለም፡፡ ልዩነቱ መንግስት ባዘጋጀው ማረሚያ ቤት መታሰርና ራሱን ማሰር ካልሆነ እንጂ፡፡

• መታሰር ማለት በአንድ በተወሰነ አከባቢ ተወስኖ መኖር ነው

• ሰውን ገድሎ፣ ሰርቆ ከሕግ ተጠያቂነት ውጪ የሚሆን የለም፡፡

• የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማረሚያ ቤቶች ድንገተኛ ጉብኝት አድርጎ ክፍተት ያለበት እንዲስተካከል ተደርጓል፡፡

• በእስር ቤት ያሉ ያነባሉ፣ ይጽፋሉ፣ ስፖርት ይሰራሉ፣ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፡፡ በግል እስር ቤት ያሉ ያን ያክል የተመቻቸ ነገር እንዳለ አላውቅም

• ሁሉም ክልሎች ወንጀለኛ ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው፤ አሳልፈው የሰጡ አሉ፣ እየፈለግን ነው ያሉም አሉ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ገድሎም ሰርቆም መጠየቁ አይቀርም፣ ከሕግ በላይ የሆነ ማንም የለም፡፡

• እንደ ብሔር ቀርቶ እንደ ቤተሰብም ሌባ የለም፣ ሌቦች ሁሉም ብሔር ውስጥ አሉ፣ ሌቦች ሲሰርቁ ማንንም አያማክሩም፣ ከሰረቀ በኋላ የእንትን ብሔር ስለሆንኩ ብሎ ወደ ብሔር ይጠጋል፡፡

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia