ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከፓርላማ አባላት ለተነሱት ጥያቄ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ዴሞክራሲን ለመገንባት መንግስት አርቆ አሳቢና ሆደሰፊ መሆን አለበት

• 20 የሚጠጉ የታጠቁም ያልጠተቁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ተመልሷል፣ ይህንን እንደ ድል ማየት ያስፈልጋል፡፡ እሱን ድል ዘንግተን ከመግባታቸው ጋር ተያይዞ የተፈጠሩ ችግሮች ላይ ማተኮር የለብንም

• የቀረበው የሰላም ጥሪ የሰላም መርህን የተከተለ ነው

• ከሁሉም ፓርቲዎች ጋር ተመሳሳይ መርህን የተከተለ ድርድር ነው የተደረገው፡፡

• ውግያ አያስፈልግም፣ ለበርካታ ዓመታት ሲንዋጋ ቆይተናል፤ የጦር መሳሪያ ድምጽ መሰመት የለበትም፣ በሀሳብ እንወያይና እናሸንፍ ነው ያልነው

• ከውጭ የገቡት ፓርቲዎች ዴሞክራሲን ለመገንባት የሚሰሩ አሉ፣ ያን የማያደርጉ አንድ እግራቸውን አዲስአባባ አንድ እግራቸውን ውጭ አድርገው የሚጫወቱ አሉ እሱ አካሄድ ውጤታማ አያደርግም፡፡

• በሀሳብ አሸናፊ ለመሆን ነው መስራት ያለብን፡፡

• ችግር እየፈጠሩ ከችግር ለማትረፍ የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ

• የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፊቷል፣ ረጅም ርቀት መሮጥ የማይችሉ ፓርቲዎች ትንፋሽ ያጥራቸዋል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ያላቸው ምርጫ ሀሳብ ወዳላቸው ፓርቲዎች ሰብሰብ ማለት ነው

• ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ዴሞክራሲ ሰላም ነው የሚንሰረው፤ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ሰላም ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነገር ሲኖር የማያደጋም እርምጃ እንወስዳለን

Via ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia