#update ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ #ዝናሽ_ታያቸው ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምናና የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና ለሁለት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረጉ፡፡ በእርዳታ ርክክብ ስነ-ስርአቱ ላይ እንደተገለጸው እርዳታው ከተደረገላቸው መካከል በጎንደር ከተማ የሚገኘው የጻዲቁ ዮሃንስ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤትና በአዘዞ ከተማ የሚገኘው የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ይገኙበታል፡፡ ለሁለቱ ትምህርት ቤቶች በእርዳታ ከተሰጡት የትምህርት ቁሳቁሶች መካከል አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት ለመስጠት የሚያስችሉ  አራት ኮምፒውተሮች ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም አራት የብሬል መጻፊያ ታይፕራይተሮችና 30 በብሬል የተዘጋጁ የማስተማሪያና የማጣቀሻ መጻህፍቶች በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለትምህርት ቤቶቹ ተበርክቶላቸዋል፡፡ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልም ለአእምሮ ታማሚዎች ህክምና አገልግሎት የሚውል የአእምሮ ነርቭ ስርአት መለኪያ መሳሪያ በእርዳታ ተሰጥቷል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia