ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ!!

ቀዳማዊት እመቤት #ዝናሽ_ታያቸው የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለተከታተሉበት የጎንደሩ ጻዲቁ ዮሐንስ 1ኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የኮምፒዩተር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በጻድቁ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያገለግል መተግበሪያ የተጫነባቸውን ሁለት ኮምፒተሮች አበርክተዋል።

በቀጣይም 20 ተጨማሪ ለዓይነ ስውራን ተማሪዎች የሚያግዙ ኮምፒዩተሮችን ለመስጠትም ቃል የገቡት ቀዳማዊት እመቤቷ በርካታ መጻሕፍትንም ለትምህርት ቤቱ አበርክተዋል።

ባለፈው መስከረም ወር ላይ በዚሁ ትምህርት ቤት የተገኙት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ60 በላይ የዓይነ ስውራን መፃፊያ መሳሪያ (ብሬይል)፣የብሬይል ወረቀት፣ የዓይነ ስውራን መምሪያ ዱላ፣ ልዩ ልዩ እስክሪብቶዎች፣ ደብተሮችንና ቦርሳዎችን ማበርከታቸው ይታወሳል።

በተጨማሪም በጎንደር ከተማ ሎዛ ማሪያም አካባቢ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስገንባት መጀመራቸን ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia