የህዳሴ ግድብ‼️

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኤልክትሮ ሜካኒክ ስራዎች በዘርፉ ዓለማቀፍ እውቅና ባላቸው የውጭ ኩባንያዎች በመሰጠቱ ህዝቡ #ጥራትን በተመለከተ ሥጋት #እንዳይገባው ተገለጸ።

ግድቡን አስመልክቶ ዛሬ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ የተሳታፊዎቹ ዋና ጥያቄ “ግድቡን እንዴት እንጨርሰዋለን እና ጥራቱስ እንዴት ይጠበቃል” የሚለው ነበር።

በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ የሰጡት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት በኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች ላይ የነበረው የዓቅም ውስንነት እንዲሁም የልምድ ማጣት ችግር ኢትዮጵያ ብዙ ገንዘብ እንድትከስር ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

አሁን ግን ለሜቴክ ተሰጥቶት የነበረው ይህ ሥራ በዘርፉ ዓለም አቀፍ እውቅና ባላቸው የጀርመን፣ የፈረንሳይና የጣሊያን ኩባንያዎች በመተካቱ ህዝቡ በዚህ ላይ ምንም ዓይነት ሥጋት እንዳይገባው አሳስበዋል።

እስካሁን ለግድቡ የወጣው 98 ቢሊዮን ብር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 10 በመቶው ከህዝብ በተገኘ ድጋፍ የተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ግድቡን አለመጨረስ አገራዊ ክስረት እንደሚያስከትል የገለጹት ኢንጂነሩ ህዝቡ የኔነት ስሜት ተሰምቶት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል
ጠይቀዋል።

እስካሁን ግድቡ 65 በመቶ መጠናቀቁን እና በ4 አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅም ተገልጿል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia