አዲስ አበባ‼️

በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን #በሚመነዝሩ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከ2 ሚሊየን የሚበልጥ የኢትዮጵያ ብር እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን #መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ታህሳስ 26 እና 27 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ኢትዮጵያ ሆቴልና ጋንዲ አካባቢ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ገንዘቦቹን መያዛቸውን ኮሚሽኑ ለfbc በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ በፊት በአካባቢዎቹ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ለምንዛሪ የተዘጋጁ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችና የኢትዮጵያ ብር መያዙን ኮሚሽኑ በመግለጫው አስታውሷል።

ሁለቱ ተቋማት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ተጠርጥረው የተያዙ አምስት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ነው ያስታወቀው።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ከባለድርሻ አካላት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ተግባሩን እንደሚቀጥል በመግለፅ፥ የከተማው ነዋሪ ይህ ጥረት እንዲሳካ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጠይቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካሥቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia