የፌደሬሽን ምክር ቤት‼️

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመከላከል የሚያስችል #ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ።

ምክር ቤቱ በማንነት ጉዳዮችና የጥያቄዎች አፈታት ላይ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ነው።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ ወይዘሮ #ኬሪያ_ኢብራሂም እንደገለጹት፤ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ምላሽ አሰጣጥ ውስንነት ነበረው።

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በማንነት ጥያቄዎች ላይ የማይመለከታቸው አካላት እጃቸውን በማስገባት ግጭት እንዲፈጠር እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

”ህገ-መንግስታዊ ስርዓት እንዲሰፍንና የህግ የበላይነት እንዲከበር በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 62 በተሰጠን ስልጣን መሰረት ለጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት እስካሁን 76 ብሔሮች ዕውቅና ያገኙ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ኬርያ በቀጣይ የ’ማንነቴ ይታወቅልኝ’ ጥያቄዎች ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ እንደሚያገኙ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡- ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia