450 #ኢትዮጵያዊያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ #ሀገር_ቤት ተመለሱ!

በሳውዲ አረቢያ ከእስር በምህረት የተፈቱ 450 ኢትዮጵያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያውያኑ የተፈቱት ከሳውዲ አረቢያ መንግስት ጋር በተደረገ ማግባባትና ድርድር እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በያዝነው ሳምንት የዛሬዎቹን ጨምሮ 2 ሺህ 400 ዜጎች በምህረት የተፈቱ ዜጎች ወደ አገራቸው ይመለሳሉ ብሏል ሚኒስቴሩ፡፡

በዛሬው ዕለትም የሳውዲ ህግ በማይፈቅዳቸው ተግባራት ላይ በመሳተፋቸው በተለያዩ የአገሪቱ ማረምያ ቤቶች በእስር የቆዩ 450 ኢትዮጵያውያን አገራቸው ገብተዋል፡፡

ተጨማሪ 450 ደግሞ የፊታችን አርብ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም ባለፈው ሳምንት ህይወታቸውን ለአደጋ ባጋለጠ ሁኔታ ቀይ ባህርን አቋርጠው ሳውዲ አረቢያ የገቡ 1500 ኢትዮጵያውያን በዚህ ሳምንት ወደ አገር ቤት ይመለሳሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳውዲ አረቢያ ጀዳህ በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በኩል ለተመላሾቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ባለፈው ሳምንት ከ410 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው መመለሱ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia