ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት ቀርበዋል‼️

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል #ተጠርጥረው ዛሬ በፌዴራሉ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት 34 ሰዎች ለነገ ተቀጠሩ።

በጎሃ አጽብሃ መዝገብ የተካተቱ ተጠርጣሪዎች ናቸው ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ለነገ የተቀጠረው።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ አቅርቦት የነበረውን አዳምጦ ከቀረቡት 36 ተጠርጣሪዎች መካከል ሁለቱ በዋስ እንዲወጡ ፈቅዷል።

16ቱ ተጠርጣሪዎች መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ለመፍቀድ ለነገ ለነገ ቀጥሯል።

ተጠርጣሪዎቹ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የማረሚያ ቤትና የፖሊስ አባልና ሃላፊ ሆነው ባገለገሉበት ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረዋል።

ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዳው ተጠርጣሪዎቹ በሽብር የተፈረጁ ግለሰቦችን በማፈን፣ ስውር እስር ቤት አስገብቶ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እንዲፈጸምባቸው ማድረጋቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በጳጉሜ 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያና ናይጄሪያ እግር ኳስ ቡድን ጨዋታ ባደረጉበት ዕለት ቦንብ አፈንድተዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በማሰቃየትና የአንድ ሰው ህይወት እንዲያልፍ ማድረግና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia